የአድዋ ድል፡ አድዋ የኢትዮጵያዊያን የአንድነት ጥግ፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌት እና የአሸናፊነት ታላቅ አሻራ ነው። ይህ ድል የተገኘው በዘመናዊ መሣሪያ ሳይሆን፣ በአፄ ምኒልክ ጥሪ፣ በእቴጌ ጣይቱ ብልሃት እና በመላው ሕዝብ የጋራ መስዋዕትነት ነው።ንጉሠ ነገሥቱ የጣልያንን ወረራ ለመቀልበስ ባደረጉት ጥሪ፣ "እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን አቆየኝ፤ ጠላቴም መጥቶ አገሬን ሊያጠፋ... ተነሥቷል። እኔም አገሬን አሳልፌ አልሰጥም" በማለት የሀገር ፍቅርን ቀስቅሰዋል። በተለይም "ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፣ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ እርዳኝ" የሚለው ቃላቸው፣ መላውን ሕዝብ በአንድ ዓላማ ስር ያስተባበረ ታሪካዊ ጥሪ ነበር።አፄ ምኒልክ ድሉን ተከትሎ "እኛ ማንም መጥቶ እንዲወረን አንፈልግም፤ የምንፈልገው በሰላም በነፃነት መኖር ብቻ ነው" በማለት የኢትዮጵያን የዘላለም ሰላም አውጀዋል