"ማህበረሰብ" ማለት በታሪክ ማህደር ባለፉት፣ ዛሬን በሚኖሩት ሕያዋንና ገና ባልተወለዱት መካከል የሚጸና ጽኑ የቃል-ኪዳን ትብብር ነው። በዚህ ትብብር ውስጥ የሚፈስ አንድ ታላቅ ትርክት አለ.. አድዋ! አድዋ የማንነታችን መሠረትና የነፃነት ብርሃን ነው። ይህ ዜማ በአባትና በልጅ ጨዋታ የታሪክን አደራ ለትውልድ ያስተላልፋል። በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የሚሰማው ኃይለኛ 'ኮረስ' የኢትዮጵያውያንን አንድነት ይዘክራል። በዋሽንትና በነጋሪት የታጀበው ድምፅ የታሪክን ገናናነትና የዛሬን ኩራት በአንድነት አሰናስሎ የሚገልጽ ድንቅ የታሪክ ዜማ ነው።Link Verification: https://suno.com/s/SXR8STymi1D6ao8P