ኢትዮጵያ የሀገር አውራ ታሪክ አለሽ የጎመራ የተላበስሽ የድል አርማ ኑሪልን በከፍታው እማማ ጥቁር ነጩ ያስዘመረ ታሪክ አለሽ የከበረ የዓለም ሀያላን ያስገረመ የጠላት ዓላማ ያከሰመ ታሪክ ፅፈሻል የማይታሰብ ያልነበረ የአለም ትርክት ድንገት የቀየረ የአድዋ ባለቤት የነፃነት ምሳሌ ከፍ በይልን ኢትዮጵያ ሁሌ ልጆች አሉሽ ለድንበርሽ የሚቆሙ በየትም ሰዓት ስትጠሪያቸው የሚሰሙ ትልቅ ትንሽ ሳይባል ሴቱ ወንዱ ለክፉ የተመኘሽ ጠላትሽን የሚያርበደብዱ ሀይል አለኝ ያለ ባህር ተሻግሮ ቢመጣ በጀግና ልጆችሽ አይቀጡ ተቀጣ አለም ጀግንነትሽ መች ሊረሳ ሁሌም ይኖራል ታሪክሽ ሲወሳ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ አለን እኛ ላንቺ አንቺም ለእኛ እንሰራለን ልጆችሽ ተባብረን በጋራ እንጠብቅሻለን ነሽና የትውልድ አደራ